ባንክ
- እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአገሪቱ ካሉት የመንግSት ባንኮች አንዱ ሲሆን በባንክ ዓለም ለይ ዋናውን ሚና እየተጫወተ የሚገኝ ባንክ ነው:: በአሁኑ ጊዜ በመላው አገሪቱ ከ330 በላይ ቅርንጫፎች ያሉት ሲሆን የመሰረታዊ የአሰራር ለውጥን በብቃት አጠናቅቆ ወደሚቀጥለው ደረጃ የደረሰ ባንክ ነው ::
- ባንኩ ይህን ሴሚናር ያዘጋጀው በወጪ ንግድ ላይ የተሰማሩ ደንበኞቹን ሰነድ ሲመረምር የታዩ ክፍተቶችን ለመዝጋት እንዲያስችል በማሰብ ነው:: እንደምታውቁት ወጪ ንግድ የውጭ ምንዛሪ ማስገኛ ዋነኛው መንገድ በመሆኑና በዚህ ንግድ ላይ የተሰማራችሁት ደንበኞቻችን ዋናውን ሚናም እንደምትጫወቱ እሙን ነው::
- ከዚህ ሴሚናር ደንበኞቻችን ባንካችን ስለሚሰጣቸው አገልግሎቶች የተሻለ ግንዛቤ ይጨብጣሉ ብለን እናምናለን:: ለእናንተም ባላችሁ የባንክ የአሰራር ዕውቀት ላይ ለመጨመር የሚያገዛችሁና ለወደፊቱም በብቃት አብንረን ለመስራት የሚያስችለንን ዕውቀት እንደሚያስጨብጣችሁ ሙሉ እምነት አለን::
የዓለም አቀፍ ንግድ አገልግሎት
- ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና የሥራ ሂደቶች አንዱ የሆነው የዓለም አቀፍ ንግድ አገልግሎት የሥራ ሂደት ዓለም አቀፍ ንግድ ማለትም የገቢና ወጪ ንግድ፣የዋስትና እንዲሁም የገቢና ወጪ ሀዋላዎች አገልግሎትን በዋናነት ይሰጣል፡፡
ይህ ክፍል ክፍያን እንዲሁም ክፍያን አስመልክቶ በንግድ አገልግሎት ላይ ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮችን ለመከላከል ይሞክራል ፡፡